BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በምዕራብ ወለጋ ስለተቃጠሉት ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ቢቢሲ በሳተላይት ምሥሎች ያደረገው ማጣራት ምን ያሳያል?
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ከዘጠኝ ያላነሱ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መቃጠላቸውን ቢቢሲ ከምንጮች እና የሳተላይት መረጃዎችን በማመሳከር አረጋግጧል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተጋሩ ቪዲዮዎች በመነሳት ቢቢሲ የሳተላይት ምሥሎችን በመጠቀም ጥቃቱ ስለተፈጸመበት ስፍራ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት ችሏል። በተጨማሪም ክስተቱን በሚመለከት መረጃ ያላቸውን እና የአካባቢው ነዋሪዎችን በማናገር ስለጥቃቱ ዝርዝር መረጃን አግኝቷል።
ቀጥታ, ጠ/ሚ ዐቢይ እና የኢራን ፕሬዝዳንት “በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች” ዙርያ መወያየታቸው ተገለጸ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስታወቁ። ሁለቱ መሪዎች በሕንድ፣ ኒው ደልሒ እየተካሄ ባለው 18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ተገናኝተው “በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት” ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የአዲስ ዓመት አከባበር ሥርዓቶች በተለያዩ የዓለም አገራት
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው። በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው። በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት አዲስ ኣመትን እንዴት ያከብሩታል?
የዓለምን ገጽታ የቀየረው የመስከረም 1 ጥቃት 25ኛ ዓመት እና የስለላው ዘርፍ ያጋጠመው ውድቅት
ለብዙ አስርተ ዓመታት የተለያዩ መሪዎች እንደተናገሩት፣ የማንኛውም መንግሥት የመጀመሪያ ግዴታ ሕዝቡን መጠበቅ ነው። በአውሮፓውያኑ 2001 መስከረም 11 ቀን ግን አሜሪካ ይህንን ግዴታ ለመወጣት ሳትችል ቀርታለች። የስለላ መረጃዎች ቢኖሩም፣ የተለያዩ ፍንጮችን በጊዜው አገናኝቶ ተግባራዊ እርምጃ የወሰደ አልነበረም።
ከ600 በላይ እስረኞች በይቅርታ ሲለቀቁ 28 ይቅርታ ባለመጠየቃቸው ሳይፈቱ ቀሩ
ከአማራ እና ከኦሮሚያ ክልሎች በከባድ ወንጀሎች ተከስሰው በፌደራል መንግሥቱ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ ከስድስት መቶ በላይ ሰዎች በይቅርታ መፈታታቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በተመሳሳይ ክስ ለዓመታት በእስር ላይ የቆዩ ነገር ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ 28 እስረኞች ደግሞ ሳይፈቱ ቀርተዋል።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል። አንዳንዶች እንደ ኢራን እና እስራኤል ላሉ አገራት የተላለፈ መልዕክት አድርገው አቅርበውታል። ሌሎች ደግሞ ይህ ስምምነት አገራቱ ለደኅንነት ዋስትና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ሙሉው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ ባለመሆኑ እየተሰሙ ያሉት መላምቶች ብቻ ናቸው።
ቪዲዮ, “ጦርነት ከተጀመረ መንግሥታት ይለወጣሉ፤ ድንበሮች ይቀየራሉ”
ቢቢሲ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ከህወሓት ጋር ያለው ውዝግብ፣ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀጠናዊ የጦርነት ስጋቶች በቃለ መጠይቁ ተዳሰዋል። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጦርነት ከተጀመረ ውጤቱ መሠረታዊ ለውጥን የሚያስከትል ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ስለኤአይ ጥቅም እና ጉዳት ምን ይላሉ?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ታደሰ ምላሽ ሰጥቷል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
አነጋጋሪ ጉዳይ
የነዋሪዎችን ሕይወት የቀጠፉት የሰሞኑ የምሥራቅ ወለጋ ጥቃቶች እና የነዋሪዎች ስጋት
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ነዋሪዎች መገደላቸውን፣ መፈናቀላቸውን እና ንብረት መውደሙ እየተነገረ ነው። ከእነዚህ ጥቃቶች ጋር የፋኖ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች እና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ስማቸው በተደጋጋሚ ይነሳል። ቢቢሲ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ምላሽ ባያገኝም ስለክስተቶቹ ነዋሪዎችን፣ የዐይን እማኞችን እና የጥቃቱ ሰለባ ቤሰቦችን አነጋግሯል።
"የማንቂያ ደወል" – በኢትዮጵያ "በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ" ያለው መድኃኒትን የሚቋቋም የወባ በሽታ
በበርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ዋነኛ የሕብረተሰብ ጤና ችግሮች መካከል አንዱ የሆነው የወባ በሽታ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃል። ይህንን በሽታ ለማከም የሚሰጠው መድኃኒት በርካቶችን ሲፈውስ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በአንዳንድ ቦታዎች ላይ መድኃኒቱ እየሠራ እንዳልሆነ እየተነገረ ነው። በዚህም የወባ በሽታው ተህዋስ መድኃኒቱን መቋቋም እየቻለ መሆኑ በጥናት ተደርሶበታል። ይህ አሳሳቢ ሁኔታ እንዴት ተከሰተ? ምንስ መፍትሔ አለው?
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የእርሻ ምርት ላይ ስጋት የፈጠረው ክስተት
ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል የተባለው ከባድ የአየር ሁኔታ ኤል ኒኖ ውጤቱ እየታየ ነው። በዚህም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ለእርሻ ሥራ ወሳኝ የሆነው ዝናብ ተዛብቷል። በአንዳንድ ቦታዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት ድርቅ ሲከሰት፣ በሌሎች ቦታዎች ደግሞ ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ ጉዳት እያደረሱ ነው። ይህ ክስተት ገና መጀመሩ ሲሆን፤ የሚያስከትለው ጉዳት ወደ ቀጣይ ዓመታትም የሚዘልቅ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል።
በቀይ ባሕር እንቅስቃሴ ላይ ስጋት የፈጠረው እና ሚሊዮኖች የሚጠየቅበት የሶማሊያ ባሕር ላይ ውንብድና
ባለፈው ሳምንት በአራት ቀናት ውስጥ ሁለት የንግድ ጭነት መርከቦች በኤደን ባሕረ ሰላጤ በባሕር ላይ ዘራፊዎች ተይዘዋል። ይህም ከዓመቱ መጀመሪያ አንስቶ የተጠለፉ መርከቦች ቁጥርን ቢያንስ 13 እንዲደርስ አድርጓል። ይህ ክስተት የባሕር ላይ ወንበዴዎችን ለመከላከል እስካሁን ታይቶ የማያውቅ የድሮን ጥቃት እንዲካሄድ ምክንያት ሆኗል።
በሳዑዲ ነሐሴ ላይ ብቻ ቢያንስ 60 ኢትዮጵያውያን ከዕፅ ጋር በተያያዙ ጥፋቶች መያዛቸውን ዘገባዎች አመለከቱ
ከዕፅ ጋር በተያያዙ ጥፋቶች የሚፈረደቸባው ሰዎችን በሞት እየቀጣች ባለችው ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ፣ በነሐሴ ወር ብቻ ጫትን ጨምሮ የተለያዩ ዕፆችን በማጓጓዝ የተጠረጠሩ ቢያንስ 60 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዘገባዎች አመለከቱ። ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም. ተጨማሪ 15 ኢትዮጵያውያን ከ290 ኪሎ ግራም ጫት ጋር መያዛቸው ተዘግቧል።
ኢዜማ ከአገራዊ ምክክሩ ጋር በተያያዘ አምስት ማሳሰቢያዎች ሰጠ
በአገራዊ ምክክሩ ላይ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ በቀጣይ የምክክር ሂደቱ ምዕራፎች መተግበር አለባቸው ያላቸውን አምስት ማሳሰቢያዎች ይፋ አደረገ። ኢዜማ፣ ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ተመካካሪዎች በሙሉ ድጋፍ ያልፈረሙባቸውን ምክረ-ሐሳቦች እንደማይቀበል ጨምሮ አስታውቋል። 4000 ተመካካሪዎችን አሳትፎ ከሐምሌ 8 ጀምሮ ከአንድ ወር በላይ የተካሔደው እና በርካታ ጥያቄዎች የተነሱበት የምክክር ሂደት ቅዳሜ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. በተካሔደ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ተጠናቅቋል።
በርካታ ምዕራባውያን አገራት "በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰሜን ኢትዮጵያ የማሸማገል ጥረት" ድጋፋቸውን ገለጹ
የአፍሪካ ኅብረት ፌደራል መንግሥት እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮችን ለማሸማገል የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ የአውሮፓ ኅብረት አባል የሆኑ የ22 አገራት እንዲሁም የዩናይትድ ኪንግደም፣ ኖርዌይ እና ካናዳ ኤምባሲዎች አስታወቁ። አገራቱ፣ "ክፉኛ በድርቅ በተጎዳው" ትግራይ ክልል የሚጀመር ወታደራዊ ግጭት ለሰሜን ኢትዮጵያ ሕዝብ "አስከፊ" እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉበት ጥቃት እንዲመረመር በደቡብ ሱዳን የሚገኘው ኤምባሲ ጠየቀ
በጁባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ሁለት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ስለተገደሉበት ጥቃት ምርመራ እንዲደረጉ ጠየቀ። የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ፣ በተፈጸመው "ደፈጣ ጥቃት" ሰላም ማስከበር ላይ የተሰማሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ሲገደሉ ሰባት ሰዎች እንደቆሰሉ አስታውቋል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
በሳምንታት ኢራንን ያንበረክካል ተብሎ ስድስተኛ ወሩን በደፈነው ጦርነት ማን ከፍተኛውን ዋጋ ከፈለ?
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመሩ ከስድስት ወራት በኋላ፣ አጭር ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ጦርነት፣ መጨረሻው ግልጽ ያልሆነ እና የተራዘመ ሆኗል። የካቲት 21/2018 ዓ.ም. እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነቱን ሲጀምሩ በሳምንታት ውስጥ እንደሚቋጭ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ጦርነቱ ጋብ እያለ አስካሁን ዘልቆ ተጽእኖው በዓለም ዙሪያ እየተሰማ ነው። በጦርነቱ ምክንያት ባለፉት ስድስት ወራት ማን ከፍተኛውን ዋጋ ከፈለ?
ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ፍርሃት የፈጠረችበት ርካሹ ድሮን
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ኢራን እየተፈጸመባት ላለው ጥቃት አጸፋውን በቀጣናው ባሉ የአሜሪካ ወዳጅ አገራት ላይ እየፈጸመች ነው። ለዚህ ደግሞ ኢራን ርካሽ እና ውጤታማ የሆኑትን ሻሂድ-136 የተባሉ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በስፋት እየተጠቀመች ነው። ይህ በምሥል እና በቪዲዮ የተደገፈው ዘገባ ስለድሮኖቹ ምንነት ይተነትናል።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
ባለ ፓስፖርት አይጦች እና ስለ ቲቢ የሚመራመሩት ኢትዮጵያዊ
አይጦች በጎ ስም የላቸውም፤ ሰዎች ከቤታቸው፣ ምግብ እና የተለያዩ እቃዎች ከሚያስቀምጡባቸው ሥፍራዎች አይጦችን ለማራቅ መርዝ ወይም መጥመድ ይጠቀማሉ። በአጠቃላይ አይጦች ከጥፋት ጋር ስለሚያያዙ በበርካቶች ዘንድ የተጠሉ ናቸው። ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ምርምር የሚያደርጉባቸው ባለ ፓስፖርት አይጦች ግን ለሰው ልጅ ጤና እና ደኅንነት ከፍተኛ ጥቅም አላቸው።
"አዳም አንድ ደራሲ የሚያስፈልጉት ሁሉም ግብዓቶች ተሟልተው ያሉት ፀሐፊ ነው"
የአዳም ረታ አዲሱ 'መዝሙረ ሄላም' የተሰኘው የረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ 1,008 ገጾች ሲኖሩት በአምስት ክፍሎች የተከፈለ ነው። ይህ የአዳም አዲስ መጽሐፍ ከዚህ ቀደም የሚጠቀማቸው እንደ ሕፅናዊነት ያሉ ሥነ ጽሑፋዊ ቴክኒኮችን የያዘ መሆኑን በመጽሐፉ አርትኦት ላይ የተሳተፈው ቢኒያም አቡራ ለቢቢሲ ተናግሯል። የመጽሐፉ መቼት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የደራሲው ሥራዎች ከ1950ዎቹ ማለቂያ እስከ 70ዎቹ መጨረሻ ያሉ ናቸው። መጽሐፉ መጠሪያ የሆነችው ሄላም ከዋና ገጸባሕሪያቱ አንዷ ስትሆን በሁሉም ክፍል ውስጥ ትገኛለች። ለሕፅናዊነት አጻጻፉ ኹነኛ ማስተሳሰሪያ በመሆን ታገለግላለች። ቢቢሲ ከአርታኢው ቢኒያም ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ. . .
አጃኢብ!
በኢትዮጵያ 55 በመቶ ሴቶች ሚስትን ለመደብደብ የሚያበቃ ምክንያት አለ ብለው እንደሚያስቡ ጥናት አሳየ
በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመደብደብ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያደረገው ጥናት አመለከተ። ሚስትን ለመምታት አሳማኝ ምክንያት እንዳለ የሚያስቡ ወንዶች ብዛት ከሴቶች ያነሰ ቢሆንም፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው አንጻር በ11 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል።


















































































